ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአንድ ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
10:48 04.07.2025 (የተሻሻለ: 11:24 04.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአንድ ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ተፈራርመዋል።
የሁለተኛው ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገት ልማት ፖሊሲ ፕሮግራም አካል የሆነው የፋይናንስ ስምምነት በእርዳታ እና በአነስተኛ ወለድና በተራዘመ ብድር መልክ የሚሰጥ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ድጋፉ የፋይናንስ ዘርፉን ለማረጋጋት፣ የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ ዘላቂ የማህበራዊ አገልግሎትን ለማረጋገጥና ሌሎች የማሻሻያውን ቁልፍ ተግባራት ለመደገፍ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X