ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት በፍጥነት የሚቆምበትን ጉዳይ በተመለከተ ለፑቲን እንዳነሱ ረዳታቸው ገለፁ

ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት በፍጥነት የሚቆምበትን ጉዳይ በተመለከተ ለፑቲን እንዳነሱ ረዳታቸው ገለፁ
ዩሪ ኡሻኮቭ በሁለቱ መሪዎች ንግግር ዙሪያ የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 ፑቲን ሩሲያ የዩክሬን ግጭት በድርድር እንዲፈታ በያዘችው አቋም እንደፀናች ለትራምፕ ገልፀዋል።
🟠 የሩሲያ መሪው ሞስኮ የግጭቱን መንስኤዎች ሁሉ መፍታት አለባቸው የሚለውን አቋም እንደማትተው ለትራምፕ አስታውቀዋል።
🟠 ፑቲን እና ትራምፕ በኢራን እና በመካከለኛው ምስራቅ አጠቃላይ ሁኔታ በዝርዝር ተወያይተዋል።
🟠 ሁለቱ መሪዎች በሶሪያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በውይይታቸው አንስተዋል፤ ሞስኮ እና ዋሽንግተን በሶሪያ ዙሪያ ውይይታቸውን ይቀጥላሉ።
🟠 በኃይል እና በህዋ ጥናት ተስፋ ሰጭ በሆኑ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶች ላይ ተወያይተዋል።
🟠 ፑቲን እና ትራምፕ በአካል ስለመገናኘት አልተወያዩም።
🟠 መሪዎቹ ግንኙነታቸውን ለመቀጠልና መነጋገር ቢፈልጉ በማንኛውም ጊዜ ስልክ ማንሳት እንደሚችሉ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
🟠 ትራምፕ በአሜሪካ ሴኔት የታክስ እና የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ በተሳካ ሁኔታ ስለመጽደቁ ለፑቲን አንስተዋል።
🟠 የሩሲያው መሪ ለመጪው የአሜሪካ የነፃነት ቀን ለትራምፕ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
🟠 ፑቲን ሩሲያ በአሜሪካ የመንግሥት ምሥረታ ትልቅ ሚና መጫወቷን አውስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X