በአዘርባጃን በስፑትኒክ ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ "መሠረተ ቢስና ሁሉንም ደንብ የጣሰ ድርጊት" ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዘርባጃን በስፑትኒክ ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ "መሠረተ ቢስና ሁሉንም ደንብ የጣሰ ድርጊት" ነው
በአዘርባጃን በስፑትኒክ ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ መሠረተ ቢስና ሁሉንም ደንብ የጣሰ ድርጊት ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.07.2025
ሰብስክራይብ

በአዘርባጃን በስፑትኒክ ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ "መሠረተ ቢስና ሁሉንም ደንብ የጣሰ ድርጊት" ነው

ጉዳዩ አዘርባጃንን ጨምሮ በትራንስ-ካውካሰስ ክልል ውስጥ “ከጊዜ ወደ ጊዜ የተባባሰ ሁኔታን” የሚያንፀባርቅ ነው ሲሉ የአሜሪካ ሕገ-መንግሥታዊ ታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኙ ዳን ላዛር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

“አሜሪካ በቅርቡ በኢራን ላይ ትልቅ ጥቃት ሰንዝራለች። ይህም በአዘርባጃን ውስጥ አለመረጋጋት በመፍጠሩ ሀገሪቱ ውስጥም የአቋም መቀያየሮችን ያስከትላል” ሲሉ ተንታኙ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ተጠቃሚዎቹ እነማን ናቸው?

ብዙ የውጭ ተዋናዮች በአዘርባጃን ውስጥ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቷን ከሩሲያ ጋር የማጋጨት ፍላጎት አላቸው” ሲሉ ምሁሩ አመልክተዋል።

እስራኤልን፣ ዩክሬንን እና አሜሪካን በመጥቀስ “ይበልጥ ጠበኛ የሆነች አዘርባጃን ሁኔታውን ለሚያካርሩት” ተዋናዮች ጠቃሚ ትሆናለች ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እንዴት ምላሽ ሰጡ?

የምዕራባውያን የሰብዓዊ መብት ማህበረሰብ ደንታ የለውም ምክንያቱም “አክራሪ ፀረ- ሩሲያ አቋም ያላቸው እና የምዕራቡ ዓለም ጥቅሞችን የሚያስጠብቁ ናቸው” ሲሉ ተንታኙ ገልጸዋል።

ለዚህም ነው በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ እነዚህ የመብት ተሟጋቾች “ሩሲያውያን የጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ብዙም የማይናገሩት" ሲሉ ላዛር ደምድመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0