በቻድ ሐይቅ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 210 የቦኮ ሃራም አሸባሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እጅ ሰጡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበቻድ ሐይቅ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 210 የቦኮ ሃራም አሸባሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እጅ ሰጡ
በቻድ ሐይቅ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 210 የቦኮ ሃራም አሸባሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እጅ ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.07.2025
ሰብስክራይብ

በቻድ ሐይቅ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 210 የቦኮ ሃራም አሸባሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እጅ ሰጡ

በናይጄሪያ ኃይሎች የሚመራው የብዝሃ-ሀገራት ጥምር ጦር በቻድ ሐይቅ ተፋሰስ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን ተከትሎ ቦል እና ባጋ ሶላ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ማርከዋቸዋል።

እጃቸውን የሰጡት አሸባሪዎች በቻድ ሐይቅ አካባቢ ጥቃቶችን ማድረጋቸውን አምነዋል ሲሉ የጥምር ጦሩ ቃል አቀባይ ኦላኒዪ ኦሶባ ገለፀዋል፡፡ በዘመቻው 10 የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት።

የጥምር ጦሩ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሙሳ ሀውሳ ወታደሮቹን ላደረጉት ጥረት አሞካሽተዋል፡፡ በአካባቢው የአሸባሪዎች መኖር በቅርቡ እንደሚያበቃ አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡ እጃቸውን የሰጡ ተዋጊዎች በሰብዓዊ እና በተሃድሶ እንደሚያዙ አረጋግጠዋል።

የቻድ ሐይቅ ክልል ገዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሳሌህ ሀጋር ቲጃኒ፤ ተመላሽ ተዋጊዎች ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ያለመ የክህሎት ሥልጠና መርሃ ግብሮች ውስጥ ይካተታሉ ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ በቻድ ሐይቅ ተፋሰስ አካባቢ ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ከቀጣናዊ አጋሮች ጋር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀግ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0