ሩሲያ እና ኒጀር አጋርነት የተቆፈረ የውሃ ጉድጓድ ተመረቀ
16:47 03.07.2025 (የተሻሻለ: 17:04 03.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ኒጀር አጋርነት የተቆፈረ የውሃ ጉድጓድ ተመረቀ
ኒያሜ አቅራቢያ በምትገኘው ሶራይ መንደር "የኒጀር - ሩሲያ ኅብረት" መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ አዲስ የውሃ መሠረተ ልማት ማክስኞ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
በድርጅቱ እና በሩሲያውያን አበርክቶት የተገነባው የውሃ ጉድጓድ የአካባቢውን ማሕበረሰብ የቆየ ፍላጎት የሚቀርፍ እንደሆነ ተነግሯል። ፕሮጀክቱ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ተደራሽነት በማሻሻል ለግብርና ሥራ፣ ለንግድ እና ለትምህርት ጊዜ የሚሰጥ እንደሆነም ነው የተጠቆመው።
ለአካባቢው ባሕላዊ መሪዎች የተላለፈው የውሃ ጉድጓድ ከኒጀር ራስን የመቻል ፕሮግራም ጋር የተጣጣመ ነው።
ይህ ፕሮጀክት በመጋቢት ወር በቲሜሬ ተመሳሳይ ፕሮጀክት በስኬት ከተጠናቀቀ በኋላ የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
