ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሥር ተጨማሪ 262.3 ሚሊየን ዶላር ተለቀቀላት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሥር ተጨማሪ 262
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሥር ተጨማሪ 262 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.07.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሥር ተጨማሪ 262.3 ሚሊየን ዶላር ተለቀቀላት

የአበዳሪው ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ሲያካሂድ የነበረውን ሶስተኛ ግምገማ ማጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ የተገለፀ ነው።

በዚህም ለኢትዮጵያ የተለቀቀውን አጠቃላይ ገንዘብ 1.873 ቢሊየን ዶላር አድርሶታል፡፡ ሀገሪቱ ከአይኤምኤፍ ጋር ሐምሌ 22፣ 2016 በደረሠችው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት መሠረት 3.4 ቢሊየን ዶላር እንደሚለቀቅላት መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡

ተቋሙ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በመተግበር ረገድ ጉልህ ለውጥ ማምጣቱን አስታውቋል፡፡

በዋጋ ግሽበት፣

በወጪ ንግድ፣

በዓለም አቀፍ ተቀማጭ ሀብት ከተጠበቀው በላይ መሻሻሎች እንደታዩ አመልክቷል፡፡

የተገኙትን ውጤቶች ለማጠናከርና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር፦

የውጭ ምንዛሪ ገበያ አሠራርን ማሻሻል፣

የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ፣

የውጭ ዕዳ ዘላቂነትን መመለስ እና

የፋይናንስ ግልጽነትን ማሻሻል እንደሚያስፈልግም ተቋሙ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0