ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የደረጃ አውጪ ኤጀንሲዎች መስፈርተሰ እንዲከለስ ጥሪ አቀረቡ
20:17 02.07.2025 (የተሻሻለ: 20:34 02.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የደረጃ አውጪ ኤጀንሲዎች መስፈርተሰ እንዲከለስ ጥሪ አቀረቡ
ሴኔጋል እርምጃውን የምትደግፈው የደረጃ አሰጣጥ አሠራሮች "ብድር የማግኘትና የመክፈል ሁኔታዎችን በእጅጉ ስለሚያወሳስቡ ነው" ሲሉ የሀገሪቱ መሪ አስታውቀዋል። አክለውም የአፍሪካን የፋይናንስ መረጋጋት ለማሻሻል የተለያዩ አማራጮችን አቅርበዋል።
ተመሳሳይ አስተያየቶች በሌሎች የአፍሪካ መሪዎችም ተንጸባርቀዋል። እንደ "ሙዲስ"፣ "ፊች" እና "ስታንዳርድ ኤንድ ፑርስ" ያሉ ኤጀንሲዎች የአፍሪካ ሀገራትን ተጨባጭ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ አያስገቡም ሲሉ ይከራከራሉ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኤጀንሲዎቹ "አድሏዊ የአሰራር ዘዴዎችን" እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል። የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ ታዳጊ ሀገራት ደረጃቸው "ያልተገባ ዝቅ እንዲል" መደረጉን አፅዕኖት ሰጥተዋል።
አፍሪካ በቅርቡ የራሷን የደረጃ አውጪ ኤጀንሲ የምታቋቁም ሲሆን በመጪው መስከረም ሥራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X