ኢትዮጵያ ‘’በሌማት ትሩፋት ወደ ምግብ ሉዓላዊነት’’
19:41 02.07.2025 (የተሻሻለ: 20:04 02.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ‘’በሌማት ትሩፋት ወደ ምግብ ሉዓላዊነት’’
ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ ያደረጉት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ካሳ በ2024/2025 ኢትዮጵያ አስምዝግባለች ያሉትን ስኬት አጋርተውናል፡፡
የወተት ምርት፦ ከ7.1 ቢሊየን ሊትር ወደ 11.7 ቢሊየን ሊትር ከፍ ብሏል፣
የዶሮ እርባታ፦ ከ100 ሚሊየን በላይ ዶሮዎች በመላ ሀገሪቱ ተሰራጭተዋል፣
የእንቁላል ምርታማነት፦ ከ3.2 ቢሊየን በእጥፍ አድጎ 7.5 ቢሊየን ደርሷል፣
ማር፦ የማር ምርት ወደ 300 ሺህ ኩንታል ከፍ ብሏል፣
የአሳ ሀብት ልማት፦ በመላው ሀገሪቱ የዓሣ ምርት በአስገራሚ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው የሌማት ትሩፋት የልማት እቅድ ብቻ ሳይሆን የምግብ ነጻነት አሻራም ጭምር ነው ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡
‘‘ይህ ኢኒሼቲቭ ለበርካታ አፍሪካ ሀገራት የለውጥ ምሳሌ ሊሆን ይችላል’’ ሲሉ ኢትዮጵያ ልምዷን የማጋራት ፍላጎት እንዳላትም አንስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
