- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ነገን ሁነኛ የኃይል አቅርቦት ማዕከል መሆን፦ የኢትዮጵያ የኤክትሪክ ኃይል ህልምና ቀጠናዊ ዕድገት

ነገን ሁነኛ የኃይል አቅርቦት ማዕከል መሆን፦ የኢትዮጵያ የኤክትሪክ ኃይል ህልምና ቀጠናዊ ዕድገት
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እንደ ጁቡቲ እና ሱዳን ላሉ ጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ታቀርባለች። ወደ ታዛንያም የሙከራ አቅርቦቱ ተጀምሯል — ሀገሪቷ የብሪክስ አባል እንደመሆኗ ከዚህ የላቀ የኃይል አቅርቦት ለማድረስ ትተጋለች።
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቀጠናዊ ሀገራት ጋር ያለው ትብብርና የጋራ ዕድገት፣ በዘርፉ ከብሪክስ አገራት በተለይም ሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ሞገስ መኮንን፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።
ኢትዮጵያ ከምታመርተው የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት አቅርቦት ስለመፍጠሯ የኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተሩ ሞገስ ሲገልፁ፦
''በዙሪያችን ያሉ ጎረቤቶቻችንን ሆነ በቀጠናው ላይ የሚገኙ ሀገራት የሀገር ውስጥ ፍላጎቶቻቸውን አሁን ላይ ማሟላት እየቻሉ አይደለም፣ ስለዚህ ይሄን የሀገር ውስጥ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ተጨማሪ ኃይል ይፈልጋሉ አንደኛው ጉዳይ ይሄ ነው። ሁለተኛው ተለዋዋጭ የሆነ የአየር ንብረት ያለበት አካባቢ ነው፣'' ብለዋል። ሞገስ አክለውም ''በተለይ ምስራቅ አፍሪካ በድርቅ ከሚጠቁ አካባቢዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን አብዛኛዎቹ ሀገራት የ ኃይል አቅርቦታቸውን የሚያሟሉት ከውኃ ከሚገኝ ኢነርጂ እንደመሆኑ መጠን ይሄ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣው ተጽእኖ፣ የኤሌክትሪክ ማምረት ላይ የሚያመጣው ደግሞ ቀጥተኛ የሆነ ጫና አለ ስለዚህ ይሄንን ጫና ለመቅረፍ ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ፣" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በዘርፉ የበለጠ ለመጎልበት ያላት እድልን በተመለከተ ሞገስ ሲገልፁ፦
''ከብሪክስ ዋነኛ መስራቾች ከአምስቱ አንዷ ሩሲያ በቀድሞ የሶቪየት ኀብረት ዘመን ኢትዮጵያ ላይ የሰሰራቻቸው የኢነርጂ ፕሮጀክቶች አሉ ለምሳሌ የመካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫን ልናነሳ እንችላለን። በሩሲያ የተሰራ ነው፣ የፋይናንስ ድጋፉም ባለሙያዎቹም ሩሲያውያን ናቸው። ስለዚህ ይሄኛውን መልሶ ለማደስ አቅሙን ለማሻሻል በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት አለ በሩሲያ በኩል እንደዛው፣'' ብለዋል።
በቆይታችን - በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ የውጭ ኢንቨስትመንት ምን ያህል ውጤታማ ነው? ከሃገር ውስጥ የሀይል አቅርቦትስ ጋር እንዴት ይጣጣማል? የኢትዮጵያ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የምስራቅ አፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ ሊቀርፁ ይችላሉን? የሚሉ መሰል ጥያቄዎችን አንስተናል።
በዚሁ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም የተዳሰሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቀጠናዊ ሀገራት ጋር ያለው ትብብርና የጋራ ዕድገት ሃሳቦችን ይከታተሉ!
አዳዲስ ዜናዎች
0