ማዳበሪያ “እየጨመረ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ አስፈላጊ ነው” ሲሉ የግብርና ልማት ኢኮኖሚስቱ ተናገሩ

ማዳበሪያ “እየጨመረ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ አስፈላጊ ነው” ሲሉ የግብርና ልማት ኢኮኖሚስቱ ተናገሩ
በአፍሪካ በፈጣን የሕዝብ ቁጥር እድገት ምክንያት እየጨመረ የመጣውን ረሃብ ለመቅረፍ ማዳበሪያን መጠቀም አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን የግብርና እና ልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ሽመልስ አርዓያ ተናግረዋል። አክለውም የማዳበሪያ ምርት የሰብል ምርት እንዲጨምር እና የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ 90 በመቶ የሚጠጋውን ድርሻ በመያዝ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር 3 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት የተፈራረመችውን ስምምነት ተከትሎ ኢኮኖሚስቱ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ የማዳበሪያ አጠቃቀም ከአጎራባች ሀገራት በእጅጉ ያነሰ መሆኑን የገለጹት ኢኮኖሚስቱ፤ ይህም የማዳበሪያ ጊዢ ውድ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ለግብርና ምርታማነትን ተግዳሮት ነው ብለዋል። ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ የማዳበሪያ አቅርቦትን ለማሳለጥ የሀገር ውስጥ ምርት አስፈላጊ እንደሆነ አፅእኖት የሰጡ ሲሆን ለዚህም ከዚህ በፊት ከገንዘብ እጥረት፣ ከባለሙያዎች እና ከመሠረተ ልማት ጋር በተያያዘ የነበሩ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ኢኮኖሚስቱ ለእንደዚህ ዓይነቱ ኢንቨስትመንት ከውጭ የሚመጣ ተቃውሞ እንዳለም ስጋታቸውን አክለው አንዳንድ አካላት ከአፍሪካ የማይቆም ድህነት አትራፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
የሀገር ውስጥ ምርት የሚከተሉትን ያስችላል፦
🟠 ባልተረጋጉ ዓለም አቀፍ ዋጋዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ይቀንሳል፣
🟠 የትራንስፖርት ወጪዎችን እና የሎጂስቲክስ ተግዳሮቶችን ይቀንሳል፣
🟠 የግብርና ምርት በማሳደግ የውጭ ምንዛሪ ያድናል፣
🟠 ኢትዮጵያን ወደፊት የማዳበሪያ ላኪ ሀገር እንድትሆን ያስችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X