አፍሪካ “በኢኮኖሚና በስትራቴጂ ደረጃ የራሷን ማንነት እየገነባች ነው” ሲሉ ናይጄሪያዊው የንግድ አማካሪ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ “በኢኮኖሚና በስትራቴጂ ደረጃ የራሷን ማንነት እየገነባች ነው” ሲሉ ናይጄሪያዊው የንግድ አማካሪ ተናገሩ

"ብዛት ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርሳችን ለመገበያየት የአሜሪካ ዶላር ላይ መወሰን እንደማያስፈልገን እየተገነዘቡ ነው" ሲሉ ባለሙያው ኦሉሴጉን ኦባሱን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በአህጉር ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የክፍያ ካርድ ስርዓት "ፓፕስካርድ" መጀመሩን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት አማካሪው፤ አፍሪካ በራሷ የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ ያላት እምነት በማደግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

"እንደ 'ፓፕስ' ያሉ ሥርዓቶች ከምዕራቡ ዓለም መፍትሄዎች ባሻገር፤ ለእኛ የሚሠሩ መፍትሄዎችን ለመገንባት ቁርጠኛ እንደሆንን ያሳያሉ" ሲሉ ባለሙያው አጽእኖት ሰጥተዋል።

የአፍሪካ የሉዓላዊነት ጥረት "ፀረ-ምዕራብ ወይም ፀረ-ዶላር" ሳይሆን አህጉሪቱን ለመደገፍ እና አፍሪካ የራሷን የወደፊት እጣ ፈንታ በራሷ መንገድ ለመቅረጽ የምታደርገው ዝግጅት አካል ነው ሲሉ ኦባሱን አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0