"ፓፕስ ካርድ፦ ለድንበር ተሻጋሪ ነፃ እንቅስቃሴ አፍሪካዊ የክፍያ ሥርዓት
14:42 02.07.2025 (የተሻሻለ: 15:04 02.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ፓፕስ ካርድ፦ ለድንበር ተሻጋሪ ነፃ እንቅስቃሴ አፍሪካዊ የክፍያ ሥርዓት
"ይህ ትልቅ ነገር ነው ። 'ፓፕስ ካርድ' ለአፍሪካውያን ኃይል መልሶ የሚሰጥ ነው... ሰዎች የሀገራቸውን ገንዘብ ተጠቅመው ድንበር ተሻጋሪ ክፍያ እንዲፈጽሙ ያስችላል። የእኛ የአፍሪካውያን ቪዛ እና ማስተርካርድ ነው። ለእኛ በእኛ የተሠራ ነው" ሲሉ በባንክ ዘርፍ የካበት ልምድ ያላቸው እና የንግድ አማካሪው ኦሉሴጉን ኦባሱን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።
ኦባሱን ፓፕስካርድ ለምን ጨዋታ ቀያሪ እንደሆኑ ሲያብራሩም፦
ግብይቶች በሀገር ውስጥ ገንዘቦች ይፈጸማሉ፣
ዋጋ እና መረጃ በአፍሪካ ውስጥ ይደብራል፣
አነስተኛ ክፍያ፣ የተሻሻለ ግላዊነት እንዲሁም ጠንካራ ኢኮኖሚ ይፈጣራል፣
ለንግድ እና ጉዞ ክልላዊ ውህደትን ይደግፋል ብለዋል።
"ይህ ገንዘቦቻችንን፣ ስርዓቶቻችንን እና ወደፊታችንን የበለጠ እንድንቆጣጠር ስለሚያደርግ በጣም ጥሩ ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X