ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ማሻሻያ እንደሚያሻቸው አሳሰበች
13:59 02.07.2025 (የተሻሻለ: 14:04 02.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ማሻሻያ እንደሚያሻቸው አሳሰበች
በተመድ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሳሙኤል ኢሳ የሪፎርም ጥያቄዎቹ የዘላቂ ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ቁልፍ እንደሆኑ ተናግረዋል።
በሲቪያ፣ ስፔን እየተካሄደ በሚገኘው አራተኛው ዓለም ዓቀፍ የልማት ፋይናንስ ኮንፍረንስ ጎን ለጎን በተካሄደ ልዩ ስብሰባ የልማት እንቅፋቶች ያሏቸውን ጉዳዮች ዘርዝረዋል፦
🟠የእዳ ጫና፣
🟠የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ እና
🟠በዓለም ላይ እየሰፋ የመጣው የሀገራት የእድገት ልዩነት።
አምባሳደር ሳሙኤል የ "ሲቪያን ስምምነት" ን መተግበር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል።
ስምምነቱ በዘላቂ ልማት ትግበራ ዙሪያ ያለውን የ4 ትሪሊየን ዶላር ዓመታዊ የፋይናንስ ክፍተት በ10 ዓመት ውስጥ ለማጥበብ ያለመ ሰነድ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X