ፑቲን ከማክሮን ጋር የስልክ ውይይት እንዳካሄዱ ክሬምሊን ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፑቲን ከማክሮን ጋር የስልክ ውይይት እንዳካሄዱ ክሬምሊን ገለፀ
ፑቲን ከማክሮን ጋር የስልክ ውይይት እንዳካሄዱ ክሬምሊን ገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2025
ሰብስክራይብ

ፑቲን ከማክሮን ጋር የስልክ ውይይት እንዳካሄዱ ክሬምሊን ገለፀ

ሁለቱ መሪዎች በኢራን እና በእስራኤል ግጭት እንዲሁም አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ በፈፀመችው ጥቃት ዙሪያ ተወያይተዋል።

የኢራንን የኒውክሌር ጉዳይ በፖለቲካዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

ፑቲን እና ማክሮን ሩሲያ እና ፈረንሳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንደ መሆናቸው ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ የሚጫወቱትን ልዩ ሚና አፅንዖት ሰጥተዋል።

የዩክሬን ቀውስን በተመለከተ ግጭቱ የምዕራባውያን ፖሊሲ ቀጥተኛ ውጤት መሆኑን ፑቲን ጠቁመዋል።

የሩሲያ መሪ ምዕራባውያን ሀገራት ለኪዬቭ የጦር መሳሪያ በማቅረብ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እያራዘሙ ነው ብለዋል።

ፑቲን የዩክሬን ግጭት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ሩሲያ መርህ ተኮረ አካሄድ እንደምትከተል አረጋግጠዋል።

በዩክሬን ግጭት ዙሪያ የሚደረግ የሰላም ስምምነት ዘላቂ፣ መሬት ላይ ባለው ሁኔታ የተመሠረተ እና የችግሩን መንስኤ የሚፈታ መሆን እንዳለበት ፑቲን ተናግረዋል።

ሁለቱ መሪዎች ከፈረንጆቹ መስከረም 2022 በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያው የስልክ ውይይት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0