የሩሲያ-አፍሪካ የእህል አጋርነት፦ ከግዢ ባለፈ ወደ ትክክለኛ የምግብ ሉዓላዊነት የሚደረግ ጉዞ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ-አፍሪካ የእህል አጋርነት፦ ከግዢ ባለፈ ወደ ትክክለኛ የምግብ ሉዓላዊነት የሚደረግ ጉዞ
የሩሲያ-አፍሪካ የእህል አጋርነት፦ ከግዢ ባለፈ ወደ ትክክለኛ የምግብ ሉዓላዊነት የሚደረግ ጉዞ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ-አፍሪካ የእህል አጋርነት፦ ከግዢ ባለፈ ወደ ትክክለኛ የምግብ ሉዓላዊነት የሚደረግ ጉዞ

"ሩሲያ በተለይም በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ምርታማነትን እና ምርትን በማሻሻል የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ በማዘመን ረገድ ለአፍሪካ ብዙ የምትሰጠው ነገር አላት" ሲሉ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር አቡሌ መሃሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ከሩሲያ ጋር ያለው የተቀራረበ ትብብር የምግብ ዋስትና እጥረት እና ድህነትን በሚከተሉት መንገዶች ሊቀንስ ይችላል፦

- የሩሲያን የግብርና ቴክኖሎጂ እና እውቀት በመጠቀም፣

- በተለይም የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራትን የምግብ ሉዓላዊነት ጥረት በመደገፍ።

"የድህረ ቅኝ አገዛዝ አስተሳሰብን ወደ ጎን በመተው…በቋሚ ተቋማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ኢኮኖሚያቸውን እንደ አዲስ በማዋቀር ሀገራት ሕዝባቸውን እንዲያሳድጉ የሚደገፉበትን መንገድ መፈለግ አለብን” ብለዋል፡፡

ተማራማሪው በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ያሻልም ብለዋል፦

- የውጭ የምግብ እርዳታ፦ ለአስርት ዓመታት የውጭ የምግብ ዕርዳታ የአፍሪካን የምግብ ስርዓት አልለወጠም።

- ዘላቂ ድጋፍ፦ በማዳበሪያ ምርት፣ በቴክኖሎጂ ተደራሽነት እና የአካባቢን ምርት ማጎልበት ላይ ሊያተኩር ይገባል።

ሩሲያ አፍሪካ ቋሚ አቅሞችን እንድትገነባ እና ጥገኝነትን እንድታቆም "እጅግ በጣም ትልቅ" ድጋፍ ልትሰጥ ትችላለች ሲሉም አክለዋል።

"የሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት የምግብ ዋስትና እጥረትን ለመቀነስ አንዱ ዋንኛ መንገድ ነው፡፡"

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንበቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0