የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በፈፀሙት ጥቃት "የፖለቲካ ህይወታቸውን እያጠፉ" ነው ሲሉ ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በፈፀሙት ጥቃት "የፖለቲካ ህይወታቸውን እያጠፉ" ነው ሲሉ ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ
የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በፈፀሙት ጥቃት የፖለቲካ ህይወታቸውን እያጠፉ ነው ሲሉ ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2025
ሰብስክራይብ

የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በፈፀሙት ጥቃት "የፖለቲካ ህይወታቸውን እያጠፉ" ነው ሲሉ ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ ተናገሩ

የአርመን መንግሥት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና ሐይማኖት ልሂቃን ተወካዮች የሚያካሂደው እስር የሀገሪቱ ባለሥልጣናት የሚከተሉት የፖለቲካ እና የርዕዮተ ዓለም ስርዓት ስሁት እንደሆነ ያሳያል ሲሉ ሀኒ ኤል-ማስሪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን በአርመን ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሐይማኖት እና የሲቪል መብቶችን የሚጥሱ በመሆናቸው የሕዝብ ተቃውሞ ሊያስነሳባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በተንታኙ ገለፃ መሠረት ፓሺንያን ይህን የሚያደርጉት፦

▪ በሕዝቡ ዘንድ እየቀነሰ የመጣውን ተቀባይነታቸውን አቅጣጫ ለማስቀየር፣

▪ በአርመን እና በሩሲያ ቤተ-ክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ፣

▪ ከአውሮፓዊ አቋማቸው ጋር በተያያዘ በዩክሬን ግጭት ለኪዬቭ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት።

ℹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በቤተ-ክርስቲያኗ መካከል ያለው ግንኙነት የተባባሰው ባለፈው ግንቦት ወር ነበር። ሰኔ 11 ቤተክርስቲያኗን ይደግፉ የነበሩት ነጋዴው ካራፔትያን በግጭቱ ምክንያት የታሰሩ ሲሆን ባለፈው አርብ ሊቀ ጳጳስ አጃፓኪያን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ዝግጅት አድርገዋል በሚል ክስ ለሁለት ወራት በቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ተወስኗል። ሊቀ-ጳጳሱ ክሱን አስተባብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0