ክሬምሊን በአዘርባጃን በስፑትኒክ እና ሩፕሊ ሠራተኞች ላይ የተፈፀመውን እስር በትኩረት እየተከታተለ እንደሆነ ገለፀ
14:53 01.07.2025 (የተሻሻለ: 15:04 01.07.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱክሬምሊን በአዘርባጃን በስፑትኒክ እና ሩፕሊ ሠራተኞች ላይ የተፈፀመውን እስር በትኩረት እየተከታተለ እንደሆነ ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ክሬምሊን በአዘርባጃን በስፑትኒክ እና ሩፕሊ ሠራተኞች ላይ የተፈፀመውን እስር በትኩረት እየተከታተለ እንደሆነ ገለፀ
ሞስኮ ከባኩ ጋር በምታደርገው ቀጥታ ግንኙነት የታሰሩት የሩሲያ ጋዜጠኞች ይፈታሉ ብላ እንደምትጠብቅ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ሀሳቦች፦
🟠 የሩሲያና ዩክሬን የድርድር ሂደት ይፋጠናል ብሎ መጠበቅ አስቸጋሪ ነው።
🟠 ሩሲያ የዩክሬን ስምምነቶች ትግበራን አታዘገይም ወይም አታቆምም።
🟠 ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሚደረጉ ድርድሮችን የማዘግየት ፍላጎት የላትም።
🟠 ሩሲያ የዩክሬን ችግር እንዲፈታ ላደረገችው ጥረት አሜሪካን ታመሰግናለች።
🟠 ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያላትን ግብ በፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማሳካት ፍላጎት አላት።
🟠 ፑቲን በዛሬው ዕለት ዓለም አቀፍ የስልክ ውይይት ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ክሬምሊን ዝርዝሩን ቆይቶ ያሳውቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X