በኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በ82 ዓመት አዛውንት ላይ የተሳካ የልብ ቀዶ ህክምና ተደረገ
12:37 01.07.2025 (የተሻሻለ: 12:54 01.07.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በ82 ዓመት አዛውንት ላይ የተሳካ የልብ ቀዶ ህክምና ተደረገ
የልብ ቀዶ ህክምና ሀኪሙ እና የቀዶ ጥገና ቡድኑ መሪ ዶክተር ፈቀደ አጉዋር ለአዛውንቷ የተደረገው የደም ቧንቧዎችን የመክፈትና የልብ በርን የመቀየር ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን በማህበራዊ ትሥሥር ገፃቸው አስነብበዋል።
ቀዶ ጥገናውን ለየት የሚያደርገው ሁለት የተለያዩ የደም ስሮችን መክፈት የሚያካትቱ ሁለት የተለያዩ ትልልቅ ቀዶ ህክምናዎች መከናወናቸው ነው ብለዋል።
ሰባት ሰዓታት የፈጀው ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ በአሁኑ ሰዓት የእድሜ ባለፀጋዋ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ዶክተሩ አመልክተዋል፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X