የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.07.2025
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባከናወነችው አመርቂ ሥራ በስንዴ ምርት ሙሉ በሙሉ ራሷን መቻሏን ገልጸዋል።

ተሰናባቹ የባንኩ ፕሬዝዳንት በስፔን ሲቬያ ከተዘጋጀው ዓለም አቀፉ የዘላቂ ልማት ፋይናንስ ኮንፍረንስ ጎን ለጎን "ድህነትን እና ረሃብን ለመዋጋት ዓለም አቀፍ ጥምረት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተናገሩት ነው።

በተጨማሪም አበዳሪው የኢትዮጵያ የሌማት ትሩፋት አካል የሆነውን የዶሮ እርባታ ፕሮጀክት በ50 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመደገፍ መወሰኑን ይፋ አድርገዋል።

በመድረኩ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፤ ሀገሪቱ በመተግበር ላይ ያለችው "የሌማት ትሩፋት ተነሳሽነት" ድህነትን ለመቀነስ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0