ኢትዮጵያ ከቢትኮይን ማይኒንግ ባለፉት አስር ወራት 55 ሚሊየን ዶላር ሰበሰበች
19:09 30.06.2025 (የተሻሻለ: 19:34 30.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከቢትኮይን ማይኒንግ ባለፉት አስር ወራት 55 ሚሊየን ዶላር ሰበሰበች
ገቢው የተገኘው በማስተላለፊያ መሠረተ ልማቶች እጥረት ምክንያት ይባክን የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለቢትኮይን ማይኒንግ በማዛወር ነው።
በዚህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአጠቃላይ ዓመታዊ ገቢው 18 በመቶ ያህሉን መሰብሰብ ችሏል።
ቢትኮይን ማይኒንግ ውስብስብ ስሌቶችን በመጠቀም የክሪፕቶ ግብይቶች የሚረጋገጡበት መንገድ ነው።
ለዚህም ቀንና ሌሊት የሚሠሩ አዳዲስ ዘመናዊ ኮምፒውተሮችን የያዙ መጋዘኖች የሚጠይቅ እንደሆነና ብዙ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚፈልግ ይነገራል።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X