ሺህ ዓመት ባስቆጠረው የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
16:24 30.06.2025 (የተሻሻለ: 16:34 30.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሺህ ዓመት ባስቆጠረው የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ
"በአርሜኒያ ያለው ሁኔታ የሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ነገር ግን ሩሲያ 'ያለ በቂ ምክንያት' የሚፈጸሙ ኢ-ፍትሐዊ ጥቃቶችን ትቃወማለች" ሲሉ ሰርጌ ላቭሮቭ በአርሜኒያ መንግሥት እና ቤተ-ክርስቲያን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት አስመልክቶ አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
"ቤተ-ክርስቲያን ሁሌም ከአርሜኒያ ማሕበረሰብ ቁልፍ ምሰሶዎች አንዷ ነች" ሲሉ የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት አፅዕኖት ሰጥተዋል።
ሩሲያ በአርሜኒያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እሁድ ተናግረዋል።
የአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሚካኤል አጃፓክያን በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተጠርጥረው አርብ ታስረዋል። የሐይማኖት አባቱ በበኩላቸው ክሱን “የፈጠራ” በማለት ውድቅ አድርገውታል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X