ኢትዮጵያ ሶስት ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከዳንጎቴ ጋር ስምምነት ላይ ደረሠች
13:18 30.06.2025 (የተሻሻለ: 13:34 30.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሶስት ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ከዳንጎቴ ጋር ስምምነት ላይ ደረሠች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ ስምምነቱ ሐምሌ ወር ላይ እንደሚጠናቀቅ አረጋግጠዋል ሲል የናይጄሪያው ቢዝነስ ዴይ ዘግቧል።
ግንባታው በሶማሌ ክልል ጎዴ በቅርቡ እንደሚጀመር ይጠበቃል።
ፋብሪካው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እና ለውጭ ገበያ ማዳበሪያ የማምረት ግብ እንዳነገበም ተነግሯል።
ናይጄሪያዊው ቢሊየኔር አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካ ከ40 ወራት በኋላ ማዳበሪያ መግዛት ታቆማለች ሲሉ በቅርቡ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X