ኪም ጆንግ-ኡን በፒዮንግያንግ ከሩሲያ የባሕል ሚኒስትር ጋር ተገናኙ
10:18 30.06.2025 (የተሻሻለ: 10:34 30.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኪም ጆንግ-ኡን በፒዮንግያንግ ከሩሲያ የባሕል ሚኒስትር ጋር ተገናኙ
የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና ወኪል እንደዘገበው የባለስልጣናቱ ውይይት እሁድ በኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄደ ሲሆን በሀገራቱ መካከል የተደረገውን አዲስ ስምምነት የመጀመሪያ ዓመት በማስመልከት መደረጉ ተገልጿል።
ኪም የባሕልና የሥነ-ጥበብ ልውውጦችን አስፈላጊነት አጉልተው ያስረዱ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ትብብርን ማስፋት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የባሕል ሚኒስትሯ ኦልጋ ሊዩቢሞቫ በኮሪያ ጉብኝታቸው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሀገሪቱን ከጃፓን ወረራ ነፃ በማውጣት ህይወታቸውን ላጡ የሶቪየት ወታደሮች ክብር ለመስጠት በፒዮንግያንግ በሚገኘው የነጻነት ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። በተጨማሪም የሩሲያ እና የሰሜን ኮሪያ የባሕል ሚኒስትሮች እ.ኤ.አ ከ2025 እስከ 2027 የሚቆይ የትብብር እቅድ መፈራረማቸውን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ