የክሮከስ ኮንሰርት አዳራሽ ጥቃት በዩክሬን እንደተቀነባበረ ፈፀሚዎቹ አመኑ
20:52 29.06.2025 (የተሻሻለ: 21:04 29.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የክሮከስ ኮንሰርት አዳራሽ ጥቃት በዩክሬን እንደተቀነባበረ ፈፀሚዎቹ አመኑ
ሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ ለ147 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት የፈፀሙቱ፤ ከጥቃቱ ጀርባ ዩክሬን እንዳለችበት በእምነት ቃላቸው እንደገለፁ ስፑትኒክ ያገኘው ማስረጃ አሳይቷል።
ከጥቃቱ በኋላ ታጣቂዎቹ ወደ ኪዬቭ ለመሸሽ አቅደው እንደነበርና እያንዳንዳቸው አንድ ሚሊየን ሩብል (12 ሺህ 743 የአሜሪካ ዶላር) ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ በዩክሬናውያን አማካኝነት የጦር መሳሪያ እንደቀረበላቸውም ገልፀዋል።
መጋቢት 13፣ 2016 ዓ.ም ታጣቂዎች ወደ ሙዚቃ አዳራሹ ገብተው በታዳሚዎች ላይ ተኩስ በመክፈት እና ቲያትር ቤቱን በእሳት በማቀጣጠል 147 ሰዎች ሲገደሉ ወደ 500 የሚጠጉ ቆስለዋል። ሦስት ተጠርጣሪዎች እስካሁን አልተገኙም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X