'ቢቢን ነፃ አውጡት'፦ ትራምፕ በእስራኤል ኔታንያሁ ላይ የቀረበው ክስ “ፖለቲካዊ” ነው አሉ
18:38 29.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 29.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'ቢቢን ነፃ አውጡት'፦ ትራምፕ በእስራኤል ኔታንያሁ ላይ የቀረበው ክስ “ፖለቲካዊ” ነው አሉ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
'ቢቢን ነፃ አውጡት'፦ ትራምፕ በእስራኤል ኔታንያሁ ላይ የቀረበው ክስ “ፖለቲካዊ” ነው አሉ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በማሕበራዊ ሚዲያ ባጋሩት ፅሁፍ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ (ቢቢ) ላይ የቀረበውን ክስ ከራሳቸው ፖለቲካዊ ውንጀላ ጋር አመሳስለውታል። ትራምፕ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የቀረቡት ክሶች "እብደት" ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
የኔታንያሁ ክሶች፦
▪መዝገብ 4000፦ በእስራኤል ትልቁን የቴሌኮም ቡድን ቤዜቅ ለተሻለ የሚዲያ ሽፋን ጉቦ በመስጠት ተከሰዋል።
▪መዝገብ 1000፦ ለሆሊውድ አዘጋጅ ፖለቲካዊ ውለታ በመዋል 300 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የቅንጦት ስጦታዎችን (ሲጋር፣ ሻምፓኝ) በመቀበል በሽንገላ እና እምነትን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል።
▪መዝገብ 2000፦ የእስራኤል ሃዮም እንቅስቃሴዎችን በመገደብ ከየዲዮት አህሮኖት ተመራጭ የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት ሙከራ በማድረግ ተከሰዋል።
የፍርድ ቤቱ ችሎት የቀጠለ ሲሆን ኔታንያሁ በሳምንት ሶስት ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ቢጠየቁም - ሂደቱ አብዛኛውን ጊዜ ተስተጓጉሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'ቢቢን ነፃ አውጡት'፦ ትራምፕ በእስራኤል ኔታንያሁ ላይ የቀረበው ክስ “ፖለቲካዊ” ነው አሉ

© telegram sputnik_ethiopia
/