የኢትዮጵያ ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ማሕበረሰብ የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጡን ተከትሎ ራሱን ለመቻል እንቅስቃሴ ጀምሯል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ማሕበረሰብ የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጡን ተከትሎ ራሱን ለመቻል እንቅስቃሴ ጀምሯል
የኢትዮጵያ ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ማሕበረሰብ የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጡን ተከትሎ ራሱን ለመቻል እንቅስቃሴ ጀምሯል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.06.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ማሕበረሰብ የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ መቋረጡን ተከትሎ ራሱን ለመቻል እንቅስቃሴ ጀምሯል

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በድንገት የገንዘብ ድጋፍ ከተቋረጠ በኋላ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የታችኛው የኦሞ ወንዝ ሸለቆ የታማ ማሕበረሰብ አካባቢ ጥበቃን በባለቤትነት ለማስተዳደር ኃላፊነት እየወሰደ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ 197 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሠፈረውን የተፈጥሮ ሀብት ከመጠበቅ ባለፈ ሕገ-ወጥ አደንና የደን ምንጠራ እንዲቀንስ አስችሎ ነበር ተብሏል።

አሁን የአካባቢው መሪዎች ገለልተኛ ምክር ቤት ለማቋቋም እና የጥበቃ ጥረቶችን ለማስቀጠል የሚያስችሉ እቅዶችን በማዘጋጀት፤ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠሩ ነው።

አስተዳዳሪው አካል በማሕበረሰቡ አባላት የሚወከሉ ተመራጮችን አካቶ ቁልፍ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ሞንጋቤ የአካባቢ ጥበቃ የዜና አውታር ዘግቧል።

የቀድሞው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የባሕልና ቱሪዝም ኃላፊ የማሕበረሰቡ ሀገር በቀል እውቀት ራስን ለመቻል እና ለማስተዳደር ጠንካራ መሠረት ነው ይላሉ።

"በስርዓቱ የተቋቋመ ቢሮ ካላቸው እና ትክክለኛ የቴክኒክ ድጋፍ ካገኙ፤ ማሕበረሰቡ አካባቢውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተዳደር ይችላል።"

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0