ብሪክስ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ ለደረሡት ስምምነት ጉልበት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሪክስ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ ለደረሡት ስምምነት ጉልበት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ተናገሩ
ብሪክስ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ ለደረሡት ስምምነት ጉልበት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.06.2025
ሰብስክራይብ

ብሪክስ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰላማዊ ኒውክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ ለደረሡት ስምምነት ጉልበት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ተናገሩ

"ኒውክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ለማዋል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ ሀገራት አሉ፤ ከዛ ውስጥ አንዷ ሩሲያ ናት። ተጨማሪ ኢነርጂ ማምረት የምንችልበትን እድል ለመደገፍ ፍላጎት አሳይተዋል። ከሩሲያ በኩል ቁርጠኝነቱ አለ፤ በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎቱ አለ። ስለዚህ አሁን ላይ በብሪክስ ግንኙነቱ የበለጠ የተሻሻለ ይሆናል የሚል እምነት አለን" ሲሉ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ ሞገስ መኮንን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አክለውም በሶቪየት ህብረት የተሠራውን የመልካ ዋካና ኃይል ማመንጫ ሩሲያ ለማደስ ፍላጎት ማሳየቷን ገልፀዋል።

"...መልሶ ለማደስና አቅሙን ለማሻሻል በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት አለ። በሩሲያ በኩልም ራሳቸው ስለሠሩት፤ እኛው ብንጠግነው የሚል ፍላጎት ስላላቸው በኢነርጂው ዘርፍ ትልቅ እድል ይዞ መጥቷል ብለን እናስባለን።"

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0