ትራምፕ ለኢራን መንፈሳዊ መሪ ክብር እንዲሰጡ አባስ አራግቺ ጠየቁ
13:28 28.06.2025 (የተሻሻለ: 13:34 28.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትራምፕ ለኢራን መንፈሳዊ መሪ ክብር እንዲሰጡ አባስ አራግቺ ጠየቁ
ትራምፕ ከቴህራን ጋር የኒውክሌር ስምምነት ለመድረስ የሚሹ ከሆነ በሚሊየን የሚቆጠሩ የአያቶላህ አሊ ካሜኔይ ታማኝ ደጋፊዎችን የሚያስከፋ ቃል መጠቀማቸውን ማቆም አለባቸው ሲሉ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢራን ተወካይ አሚር ሰኢድ ኢራቫኒም እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ ካሜኔይ ላይ የሰነዘሩትን ዛቻ ድርጅቱ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።
"ከፍተኛ ባለሥልጣናት በግድ የለሽነትና ሆን ብለው የሰነዘሩት ማስፈራሪያ የአንድ ሀገር ፖለቲካዊ ነፃነት ወይም የግዛት አንድነት ላይ ስጋት መፍጠር ወይም ኃይል መጠቀም የሚከለክለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር በግልፅ የሚጥስ ነው" ሲሉ ተወካዩ በድብዳቤያቸው ላይ አስፍረዋል።
ትራምፕ ካሜኔይ የት እንዳሉ "በትክክል ያውቁ እንደነበር፤ ነገር ግን ለአሜሪካ እና እስራኤል ጦር እንዳይገደሉ ትዕዛዝ በመስጠታቸው አያቶላውን "ከአሰቃቂ ሞት" እንደታደጉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X