- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የምዕራባዊያን 'ጠንካራ የኃይል ስልት'በአፍሪካ – አዲሱ የዳግም ቅኝ ግዛት ወጀብ?

የምዕራባዊያን 'ጠንካራ የኃይል ስልት'በአፍሪካ – አዲሱ የዳግም ቅኝ ግዛት ወጀብ?
ሰብስክራይብ
የማረጋጋት ተልዕኮዎች ወደ ረጅም ጊዜ የወታደራዊ ሰፈራ፣ የዕዳ ወጥመድ እና አስገዳጅ የዲጂታል ቁጥጥር ስርዓቶች ተቀይረዋል።
ምዕራባዊያን በአዲስ መልክ አፍሪካን ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ ይሆን?
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለምዕራባዊያን ጠንካራ የኃይል ስልትና ስለዳግም ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት ክቡር ገና - የኢኒሼቲቭ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተርን ጋብዟቸዋል።
የምዕራባዊያን ልዩ ስትራተጂዎችን በተመለከተ ክቡር ገና ሲያብራሩ፡-
በማረጋጋት ተልዕኮ ላይ የኔቶ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስፈን ተልዕኮዎች ወደ ረጅም ዘመን የወታደራዊ ሰፈራነት ተለውጠዋል። ይህ ደግሞ በማሊና ሶማሊያ ተመልክተናል - ሲሉ ተናግረዋል።
ሁሉን አቀፍ የዓለም ስርዓት ስላለው ጠቀሜታ ክቡር ገና ሲያስረዱ፡-
''ሁሉን አቀፍ ዓለም የምዕራባዊያን የተናጥል ዋልታን በማስጣል አፍሪካን በእጅጉ ተጠቃሚ የሚያደርግ ጉዳይ ነው''  ብለዋል። አክለዉም ''የአፍሪካ አህጉር የነፃ ገበያ ስምምነት የምዕራባዊያን የተናጥል ዋልታን ለማመጣጠን ሁነኛ መፍትሔ ይሰጣል። [በዚህ ውስጥ]  የአፍሪካ የክፍያ ስርዓት ደግሞ ሌላኛው ነው። ምክንያቱም በዶላር ላይ ያለ ጥገኝነትን ለአፍሪካ ይቀንሳል'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 
ለዚህም አፍሪካ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ያስፈልጋታል ፣ የደቡባዊዉ ዓለም የመረጃ ምንጮች ደግሞ የምዕራቡን ዓለም የሃሰት ዘመቻዎች በመመከት የአፈሪካ መከታ ሆነዋል።
''ትልልቅ መገናኛ ብዙሃን ፈተና እየሆኑ መምጣታቸው ግልፅ ነው፤ [...] ዜጎች አማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ሲኖራቸው ሌሎች ወይም በሌላ ወገን ካለው ሚዲያ ሃሳብን ይሸምታሉ። አሁን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኑን ፈተናዎችን የምንመክትበት አማራጭ አለን ፣ በእርግጥም ስፑትኒክም ሆነ ሲጂቲኤን የምዕራቡን አለም ፕሮፓጋንዳ የሚገቱ  አማራጮች ናቸው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በዚሁ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕርግራም ይህንኑ እና ስለአፍሪካ የግምገማ ስርዓትና አስፈላጊነት የተነሱ ሃሳቦችን ይከታተሉ!
አዳዲስ ዜናዎች
0