ኢትዮጵያ ተገማችና ግልፅ የእዳ እፎይታ አሠራር አስፈላጊ እንደሆነ ገለፀች
16:06 27.06.2025 (የተሻሻለ: 16:24 27.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ተገማችና ግልፅ የእዳ እፎይታ አሠራር አስፈላጊ እንደሆነ ገለፀች
በፈረንሳይ በተካሄደው 12ኛው የፓሪስ ፎረም ላይ በገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካለኝ የተመራ ልዑክ ተሳትፏል።
ባለሥልጣኑ በአበዳሪ እና ተበዳሪ ሀገራት መካከል ግልጽነትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት በሀገራት ዕዳ አቀናነስ ላይ የጋራ ኃላፊነት ስሜት እንዲኖር ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የዕዳ ማስተካከያ እየተደረገላት ሲሆን በመጋቢት ወር ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ይፋዊ የመርህ ስምምነት ደርሳ፤ የመግባቢያ ሰነዱ በቅርቡ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X