የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ ኢትዮጵያ ገብተዋል
10:36 27.06.2025 (የተሻሻለ: 10:54 27.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግብዣ ኢትዮጵያ ገብተዋል
ካሺም ሼቲማ አዲስ አበባ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ባለሥልጣኑ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በተመረጡ የሀገሪቱ ክልሎች ቁልፍ የኢንዱስትሪ ዞኖች እና የግብርና ተቋማትን እንደሚጎበኙ የናይጄሪያ ሚዲያ ዘግቧል።
በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ማስጀመሪያ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያን ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት እንደሚያጠናክር ታምኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/