በኢትዮጵያዊ ወጣት የበለፀገው የተጠቃሚ ማረጋገጫ ሶፍትዌር አምስት ሚልየን ዶላር የመነሻ ካፒታል አገኘ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያዊ ወጣት የበለፀገው የተጠቃሚ ማረጋገጫ ሶፍትዌር አምስት ሚልየን ዶላር የመነሻ ካፒታል አገኘ
በኢትዮጵያዊ ወጣት የበለፀገው የተጠቃሚ ማረጋገጫ ሶፍትዌር አምስት ሚልየን ዶላር የመነሻ ካፒታል አገኘ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.06.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያዊ ወጣት የበለፀገው የተጠቃሚ ማረጋገጫ ሶፍትዌር አምስት ሚልየን ዶላር የመነሻ ካፒታል አገኘ

ቤተር አውት የተሰኘው ስታርትአፕ በአበልፃጊዎች ምርጡ የማረጋገጨ መሳሪያ እየተባለ እንደሚገኝ ቴክ ክራንች ዘግቧል።

ነጻ መተግበሪያ የሚጠቀመው ሶፍትዌር አበልፃጊዎች የተጠቃሚዎች ማረጋገጫ የሚያስተዳድሩበትን መንገድ በማቅለሉ ተወዳጅ ሆኗል።

ባለፈው ዓመት ወደ ሥራ የገባው የማረጋገጫ ማዕቀፍ በየሳምንቱ ከ150 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች እንደሚጭኑት መስራቹ በረከት እንግዳ ተናግሯል።

የዲጂታል ስርዓቱን ለብቻው በራሱ ጥረት እንዳበለፀገ የሚገልፀው በረከት፤ ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘቱ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የሚበረታታ እንደሆነ አንስቷል።

"ዓለም አቀፍ ምርት የሚመሠርቱ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሉም። ለብዙዎች በጭራሽ የማይቻል ይመስላቸዋል። ስለዚህ ትኩረት ማግኘቱ ሌሎች ሰዎችም እንዲጥሩ ያነሳሳል" ብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0