የኢራን እና እስራኤል ግጭትን በተመለከተ የዛሬ ምሽት መረጃዎች፦
20:29 26.06.2025 (የተሻሻለ: 20:34 26.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራን እና እስራኤል ግጭትን በተመለከተ የዛሬ ምሽት መረጃዎች፦
▪ትራምፕ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ስለሰነዘረችው ጥቃት መረጃ ካወጡ በኋላ “መሰሪ ዓላማ” አላቸው በማለት የሲኤንኤን እና የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢዎች ከሥራ እንዲባረሩ ጠይቀዋል።
▪ኢራን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መርማሪዎች የኒውክሌር አቅሟን እንዲፈትሹ እንድትፈቅድ ተቋሙ ጠይቋል።
▪ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው የአውሮፓ ሀገራት የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የበለፀገ ዩራኒየም ክምችት አላወደመም ብለው ያምናሉ።
▪ቴህራን እስራኤልን ድል እንዳደረገች ብቻ ሳይሆን፤ ከአሜሪካ ጋር ባላት ግጭትም የበላይነትን አግኝታለች ሲሉ አያቶላው ተናግረዋል።
▪የኢራን ጋርዲያን ካውንስል ከአቶሚክ ኤጀንሲው ጋር ትብብር የሚያስቆም ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።
▪የዩናይትድ ስቴትስ የጋራ ወታደራዊ እዝ ሊቀመንበር ዳን ኬይን “ሚድናይት ሃመር” የሚል ስያሜ ሰጥታ አሜሪካ በኢራን ላይ የሰነዘረችው ጥቃት የ15 ዓመታት እቅድ ውጤት ነው ብለዋል።
▪የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥረቶችን በማዳከም እና የኒውክሌር ስርጭት መከላከያ ስምምነትን በመቃወም አሜሪካን እና እስራኤልን ወንጅለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X