የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰጧቸው የቅርብ መግለጫዎች፦
19:56 26.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 26.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰጧቸው የቅርብ መግለጫዎች፦
▪ሩሲያ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው የተኩስ አቁም ወታደራዊ ውጥረቱን ያቆማል ብላ ተስፋ ታደርጋለች።
▪ኢራን ላይ ጥቃቶችን ለማቀድ እንደ መረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለገለው የዓለም ዓቀፉ አቶሚክ ኢጀንሲ የማረጋገጫ ስርዓት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።
▪ወደ ድርድር ለመመለስ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለውን የተኩስ አቁም ማስቀጠል እና ማጠናከር አስፈላጊ ነው።
▪ሞስኮ በኢራን እና በአቶሚክ ኤጀንሲው መካከል በነበረው ትብብር ላይ የደረሰው ጉዳት እንደሚጠገን ተስፋ ታደርጋለች፤ ለዚህም በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው።
▪የኔቶን የመከላከያ ወጪ ለመጨመር የተወሰነው ለ"ሩሲያ ስጋት" ምላሽ ነው ቢባልም፤ በእውነቱ አሜሪካን ለማስደሰት የተደረገ ነው።
▪የጀርመን አምባሳደር በቅርቡ ወደ ሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርተው በበርሊን በሩሲያ ጋዜጠኞች ላይ ለተወሰዱት እርምጃዎች የአጸፋ እርምጃ እንደሚከተል ይገለጽላቸዋል።
▪የሩሲያ እና ዩክሬን አዲስ ዙር ድርድር የሚካሄድበት ቀን በልዑካን ቡድን መሪዎች ይወሰናል፤ ከእነሱ መረጃ ይጠበቃል።
▪ሞስኮ ኢስታንቡል በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ለሚደረጉ ድርድሮች መድረክ ሆና እንደምትቀጥል ታምናለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X