የሊቀ ጳጳስ ባግራጥ ጋልስታንያን እስር "የአርሚኒያ መንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ጥላቻ" ያሳያል ሲሉ ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሊቀ ጳጳስ ባግራጥ ጋልስታንያን እስር "የአርሚኒያ መንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ጥላቻ" ያሳያል ሲሉ ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ተናገሩ
የሊቀ ጳጳስ ባግራጥ ጋልስታንያን እስር የአርሚኒያ መንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ጥላቻ ያሳያል ሲሉ ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.06.2025
ሰብስክራይብ

የሊቀ ጳጳስ ባግራጥ ጋልስታንያን እስር "የአርሚኒያ መንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ጥላቻ" ያሳያል ሲሉ ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ተናገሩ

በአርሜኒያ ሊቀ ጳጳስ ባግራጥ ጋልስታንያን እንዲሁም ሳምቬል ካራፔትያን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ኒኮል ፓሺንያንን በመቃወማቸው መታሠራቸው ምዕራባውያን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጫና የማሳደር ሙከራቸው አካል ነው ሲሉ ዲያቆን ጥላሁን ጎሹ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

"እንደዚህ ዓይነት ተግባራትን በዩክሬንና ሞልዶቫ አይተናል። እንደምታውቁት ኦርቶዶክስ የምዕራቡን ዓለም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና የመሳሰሉትን አትፈቅድም። ስለዚህ ምዕራባውያን የራሳቸውን መጥፎ አጀንዳ ለማስፋት ቤተ-ክርስቲያንን ማፍረስ አለባቸው። የአርሜኒያ ቤተ-ክርስቲያንን ወደ ምዕራብ እየተጠጋ ባለው መንግሥት ስር ለማድረግ እየተሞከረ ካለው ጥረት አንዱ ነው ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነትና ጸረ-ሩሲያ ፖሊሲዎችን የሚቃወሙ ሁሉ ጦርነቱ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም እንደሆነም ሊገነዘቡ ይገባል ሲሉም አፅዕኖት ሰጥተዋል።

"ሩሲያ የባሕላዊ እሴቶች ዘብ በመሆኗ በተለይም በኦርቶዶክስ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ከመቼውም ጊዜ በላይ ማጠናከር  አስፈላጊ ነው" ሲሉም አስገንዝበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0