እንደ ብሪክስ ያሉ ጥምረቶች ለኢትዮጵያ እድገት ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ፤ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አሥራት ተናገሩ
17:46 26.06.2025 (የተሻሻለ: 19:04 26.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
እንደ ብሪክስ ያሉ ጥምረቶች ለኢትዮጵያ እድገት ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ፤ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አሥራት ተናገሩ
ድጋፉ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በፋይናንስ ድጋፍ፣ በፖሊሲ ምክክር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ሊሆን እንደሚችልም ሚኒስትር ዴኤታው በሦስተኛው ዓለም አቀፍ "የቢግ 5 ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ" ዓውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
"እንደ ብሪክስ ያሉ ጥምረቶች ኢትዮጵያን የመሰሉ ሀገራት እንደ ሩሲያ፣ ቻይና እና ብራዚል ካሉ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች ልምድ ለመቅሰም ያስችላቸዋል" ብለዋል።
ብሪክስ በአባል ሀገራቱ መካከል የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግበት "እንደ አዲሱ የልማት ባንክ ያሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች እና ስልቶች አሉት" ያሉት የትምጌታ አሥራት፤ ለኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እንደምትጠብቅ ጠቁመዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ሀገሪቱ ሩሲያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ኩባንያዎችን በደስታ ለመቀበል ዝግጁ መሆኗንም አመላክተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X