በአዲስ አበባ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር መጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ተባለ
13:46 26.06.2025 (የተሻሻለ: 14:04 26.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር መጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ 7 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር መጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ተባለ
ከአዲሱ የአቃቂ–ቦሌ የጭነት መንገድ እና ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን አቅራቢያ የተገነባው የኢንዱስትሪ መንደር፤ 93 ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን ከ120 በላይ የማምረቻ እና የኤግዚቢሽን ሼዶችንም አካቷል።
🟠ለብረታብረት ሥራ፣
🟠ለእንጨት ውጤቶች፣
🟠ለጨርቃ ጨርቅ፣
🟠ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣
🟠የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት ይውላል ተብሏል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ የጅምላ ሥራ ፈጠራን ለማነሳሳት፣ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪን ለማነቃቃት እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች በመተካት የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታት ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
