ኢትዮጵያ የባንኩን ዘርፍ በይፋ ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ባለሀብቶች ከፈተች
12:24 26.06.2025 (የተሻሻለ: 12:34 26.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የባንኩን ዘርፍ በይፋ ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና ባለሀብቶች ከፈተች
በ3.4 ቢሊየን ዶላር የአይኤምኤፍ ስምምነት የተደገፈው እና የሀገሪቱ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተነሳሽነት አካል የሆነው ይህ እርምጃ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ያለመ ነው።
ማሻሻያው የገንዘብ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረግ እና 8.4 ቢሊየን ዶላር የሚደረሰውን የሀገሪቱን ዕዳ ማሸጋሸግ ያካትታል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባንኮች ተቀጥላዎች፣ ቅርንጫፎች እና እንደራሴ ቢሮዎች እንዲከፍቱ ወይም በሀገር ውስጥ ባንኮች ውስጥ አክሲዮን እንዲገዙ የሚያስችለውን ሕግ በታህሳስ ወር አጽድቃለች።
ተጨማሪ መመሪያ ግን የውጭ ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በሀገር ውስጥ ባንኮች ከ40% በላይ ድርሻ እንዳይገዙ ይገድባል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X