ብሪክስ ፑቲን ያቀረቡትን ዓለም አቀፍ የዕድገት መድረክ የማቋቋም ሃሳብ እየመከረበት እንደሆነ የክሬምሊን አማካሪ ተናገሩ
10:42 26.06.2025 (የተሻሻለ: 11:04 26.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሪክስ ፑቲን ያቀረቡትን ዓለም አቀፍ የዕድገት መድረክ የማቋቋም ሃሳብ እየመከረበት እንደሆነ የክሬምሊን አማካሪ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ብሪክስ ፑቲን ያቀረቡትን ዓለም አቀፍ የዕድገት መድረክ የማቋቋም ሃሳብ እየመከረበት እንደሆነ የክሬምሊን አማካሪ ተናገሩ
አማካሪው ዩሪ ኡሻኮቭ መድረኩ ለምዕራባውያን ግሎባሊዝም ምትክ የመሆን እድል ይኖርው ይሆን በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ ጉዳዩ ብራዚል በሚካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ የውይይት ርዕስ እንደሚሆን ገልጸዋል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የንግድ፣ የሎጂስቲክስ፣ የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የኢንቨስትመንት ዘርፎችን የሚያሰባስብ አዲስና ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የዕድገት መድረክ እንዲቋቋም በ #SPIEF2025 ጉባኤ ላይ ጥሪ አቅርበዋል።
ዓላማው የቆዩ የግሎባላይዜሽን ሥርዓቶችን ማዘመን ሳይሆን ብሔራዊ ጥቅሞችን የሚያከብር አዲስ የልማት ሞዴል መገንባት እንደሆነ ተናግረዋል። አጋር ሀገራት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X