በእስራኤል እና በአሜሪካ የተካሄዱ ጥቃቶች የመካከለኛውን ምሥራቅ ሁኔታ በእጅጉ አባብሰውታል ሲሉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ገለፁ
10:30 26.06.2025 (የተሻሻለ: 10:54 26.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በእስራኤል እና በአሜሪካ የተካሄዱ ጥቃቶች የመካከለኛውን ምሥራቅ ሁኔታ በእጅጉ አባብሰውታል ሲሉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ገለፁ
ሚኒስትሩ አንድሬ ቤሎሶቭ ዓለም አቀፍ ወታደራዊ-ፖለቲካዊ ሁኔታዎች አሁንም ፈታኝ ሆነው መባባሳቸውን በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
🟠 አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ያደረሱት ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን በግልጽ የጣሰ ነው፡፡
🟠 ሩሲያ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አሸማጋይ ለመሆን ፈቃደኛ ነች፡፡
🟠 የሽብር ርዕዮተ ዓለም መስፋፋት እና ታጣቂዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ ወደ አፍጋኒስታን መፍለሳቸው ቀጥሏል፡፡
🟠 የዓለምን መረጋጋት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሚናቸው እጅግ በጣም ተዳክሟል።
ዩክሬን፦
🟠 የሩሲያ ጦር በሰሜን ምስራቅ ወታደራዊ ዲስትሪክት ውስጥ የተሳካ የማጥቃት ዘመቻ እያካሄደ ነው፡፡
🟠 የኪዬቭ አገዛዝ ሽንፈቱ የማይቀር መሆኑን በመረዳቱ በሽብር ድርጊቶች ላይ እየተማመነ ነው፡፡
🟠 ሩሲያ ግጭቱን ለማቆም ፈቃደኛ እንደሆነች ደጋግማ ገልጻለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X