በኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የእሮብ ምሽት መረጃዎች፦
20:09 25.06.2025 (የተሻሻለ: 20:24 25.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ የእሮብ ምሽት መረጃዎች፦
▪ ፔንታጎን በኢራን ላይ በተሰነዘሩት ጥቃቶች የደረሰውን ጉዳት መጠን እስካሁን እንደማያውቅና ከእስራኤል መረጃ እየጠበቀ መሆኑን ገልጿል።
▪ስለ ኢራን የኒውክሌር ተቋማት ማንም እውነተኛ መረጃ ያለው አይመስልም ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
▪ ኢራን የኒውክሌር መሠረተ ልማቷን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል እውቀትና አቅም አላት ሲሉ የዓለም አቀፉ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኃላፊ አስታውቀዋል።
▪ ኢራን ዓለም አቀፉን ኢንተርኔት መልሳ መጠቀም ጀምራለች።
▪ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስፋሃን የሚገኘው የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲሉ ተናግረዋል።
▪ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኔቶ ዋና ፀሐፊ ለትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መላካቸውን "አሳፋሪ" ሲል ገልጾታል።
▪ ትራምፕ ኢራን እና እስራኤል ጦርነታቸውን በቅርቡ ዳግም ሊጀምሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X