የአዲሱ 4++ ትውልድ ኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች የሩሲያ ጦር ኃይሎችን ተቀላቀሉ

ሰብስክራይብ

የአዲሱ 4++ ትውልድ ኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች የሩሲያ ጦር ኃይሎችን ተቀላቀሉ

ጄቶቹ የተለያዩ ተከታታይ የፋብሪካ ሙከራዎችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀው ወደሚሰማሩበት የጦር ሠፈር አምርተዋል።

በተባበሩት አውሮፕላን ኮርፖሬሽን የተገነቡት የኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች ቁልፍ ባህሪያት፦

ሚና፦

በአየር የበላይነትን ለመቆጣጠር እና የመሬትና የባሕር ላይ ኢላማዎችን ለማውደም ታስቦ የተሠራ ነው።

የአሠራር ሁኔታዎች፦

ጄቱ በቀንና በሌሊት በሁሉም የአየር ሁኔታዎች እና በሩቅ ርቀት ላይ ውጤታማ በሆነ መንገድ መብረር ይችላል።

አቅሞች፦

ጄቱ እጅግ በጣም ብዙ የጦር መሳሪያዎች፣ የላቁ የአብራሪነት ክህሎቶች እና የተራቀቁ የአሰሳ እና ኢላማ መሳሪዎች አሉት።

ግዙፉ የሩሲያ የኢንዱስትሪ ሮስቴክ ከፍተኛ ባለሥልጣን ቭላድሚር አርቲያኮቭ "ወታደራዊ አብራሪዎች የጄቱ አፈጻጸም በእጅጉ አድንቀዋል። ይህ ጄት በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት በደረጃው የበላይ እንደሆነ አስመስክሯል" ብለዋል።

የኮርፕሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቫዲም ባዴካ በፈረንጆቹ 2030 የሰው ኃይል ምርታማነትን በ30% የማሳደግ እቅድ መያዙን አስታውቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአዲሱ 4++ ትውልድ ኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች የሩሲያ ጦር ኃይሎችን ተቀላቀሉ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአዲሱ 4++ ትውልድ ኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች የሩሲያ ጦር ኃይሎችን ተቀላቀሉ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የአዲሱ 4++ ትውልድ ኤስዩ-35ኤስ ተዋጊ ጄቶች የሩሲያ ጦር ኃይሎችን ተቀላቀሉ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0