- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ሉዓላዊነትን እና ትብብርን ማዳበር፡ የአፍሪካ የግብርና ለውጥ ሥር እየሰደደ ነው

ሉዓላዊነትን እና ትብብርን ማዳበር፡ የአፍሪካ የግብርና ለውጥ ሥር እየሰደደ ነው
ሰብስክራይብ
“የትሮፒካል ክልል [የደቡባዊ ዓለም] ሀገራት ድህነትን እና ረሃብን በጋራ ለመጋፈጥ አንድ ላይ መሆን በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” ሲሉ የብራዚል የግብርናና የእንስሳት እርባታ ም/ ሚኒስትር ክሌበር ሶአሬስ ከ7ኛው የአግሮ ፉድ ኢትዮጵያ ሁነት በጎንዮሽ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ጥምረትም ዓለም ለገጠመው የድህነት እና ረሃብ ''ችግሮችን ለመቋቋም የBRICS ጥምረት ምርጡ እንቅስቃሴ ነው።'' ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ''በእርግጥ ብራዚል ኢትዮጵያን በዚህ እንቅስቃሴ እንድትሳተፍ ስትጋብዝ፣ ኢትዮጵያ በጣም ጠቃሚ መሪ በመሆኗ እና በአፍሪካ እና በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው አመራርነት ሚና ስላላት ነው። [የብራዚል ግብዣ] መሰል ፈተናዎችን ለመቅረፍ በጋራ ለመስራት ስላሰብን ነው'' ሲሉ ተናግረዋል።
🎤 ሌሎች ቁልፍ ምልከታዎችን ፦
ዶ/ር ፋቢያና ቪላ አልቬስ ፦ በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ የግብርና ጉዳይ አታሼ
አያልነህ አባዋ ፦ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብሔራዊ ፕሮግራም አስተባባሪ እና ዳይሬክተር
ሰናይት መብሬ ፦ የኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ፀጋዬ አበበ ፦ ሆርቲካልቸር ሥራ ባለቤት እና
ያሬድ ፀጋዬ ፦ የሶላር ላይፍ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር የተደረገውን ቆይታ ይከታተሉ።
የምግብ ሉዓላዊነት :- አፍሪካ በምግብ ራሷን ለመቻል ሀገርኛ የሰብል ዝርያዎችን መጠበቅ እና ዳግም ሊዘሩ ከማይችሉ የሰብል ዝርያዎች ተፅዕኖ ነፃ መሆኗን ማረጋገጥ የግድ ይላታል።
ሃሳቡን በጥልቀት ለመረዳት ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተሉ!
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ AfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0