የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቁስል ህክምናና ለቆዳ እንክብካቤ የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት የሚያግዙ ንጥረ ነገሮችን በምርምር እያውጣሁ ነው አለ
17:57 25.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 25.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቁስል ህክምናና ለቆዳ እንክብካቤ የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት የሚያግዙ ንጥረ ነገሮችን በምርምር እያውጣሁ ነው አለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቁስል ህክምናና ለቆዳ እንክብካቤ የሚውሉ ምርቶችን ለማምረት የሚያግዙ ንጥረ ነገሮችን በምርምር እያውጣሁ ነው አለ
በዩኒቨርስቲው ስር የሚገኘው የሲዲቲ አፍሪካ የምርምር ማዕከል በሀገር ውስጥ መድኃኒት የማምረት አቅምን የሚያሳድጉ የምርምር ውጤቶችን እያፈለቀ መሆኑን አስታውቋል።
ተቋሙ ሀገር ላይ የሚደርሰውን የምጣኔ ሀብት ጫና ለመቀነስና የማምረት አቅምን የበለጠ ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ የማዕከሉ የድራግ ዲቨሎፕመንት ቡድን መሪ ዶክተር በለጠ አደፍርስ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ አብራርተዋል።
ማዕከሉ የመድኃኒት፣ የክትባትና የመመርመሪያ ኪቶች በሀገር ውስጥ እንዲሁም በአፍሪካ እንዲመረቱ ምርምር፣ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ ጨምረው ገልፀዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X