በናይሮቢ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በትንሹ 10 ሰዎች በጥይት ተመቱ
17:20 25.06.2025 (የተሻሻለ: 17:34 25.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በናይሮቢ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በትንሹ 10 ሰዎች በጥይት ተመቱ
ሕግ አስከባሪዎቹ ሁከት ፈጣሪ አክቲቪስቶችን ለመበተን ተኩስ ለመክፈት መገደዳቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
መገናኛ ብዙሃኑ ጭንቅላቱ ላይ የመቁሰል አደጋ ያጋጠመው የፖሊስ አባል ጨምሮ በተቃውሞው የተጎዱ ሰዎችን ወደ ጆሞ ኬንያታ ብሔራዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውን አስታውቀዋል።
የዛሬው ሰልፍ በሀገሪቱ የታክስ ጭማሪን እንዲሁም የፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አመራርን በመቃወም ሰልፍ የተጀመረበትን አንደኛ ዓመት በማስታወስ የተካሄደ ስለመሆኑ ተነግሯል። ባሳለፍነው ዓመት በዛሬው ዕለት ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፓርላማ እና የከተማዋ ምክር ቤት ህንጻዎች ላይ እሳት ለኩሰው ነበር። ለሁለት ሳምንታት በዘለቀው ተቃውሞ 39 ሰዎች ሲገደሉ ከ350 በላይ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ የኬንያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።
ተቃውሞውን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ አወዛጋቢውን የታክስ ሕግ ቢያነሱም መንግሥታቸው 7.7 ቢሊየን ዶላር ከውጭ ገበያ ለመበደር ሊገደድ እንደሚችል ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ © telegram sputnik_ethiopia
/