የማሊ ፕሬዝዳንት በሩሲያ ታታርስታን ግዛት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
17:04 25.06.2025 (የተሻሻለ: 17:24 25.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የማሊ ፕሬዝዳንት በሩሲያ ታታርስታን ግዛት ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
አሲሚ ጎይታ ዛሬ ከግዛቱ መሪ ሩስታም ሚኒካኖቭ ጋር ለመገናኘት ነው ታታርስታን ሪፐብሊክ የገቡት፡፡
በዋና ከተማዋ ካዛን አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሚኒካኖቭ እና በሩሲያ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ዩኑስ-ቤክ የቭኩሮቭ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የማሊው መሪ ባሕላዊ የሩሲያ ምግቦችን (ዳቦ ከጨው ጋር) እና የታታር ምግቦችን (ቻክ-ቻክ፤ የተጠበሰ የኬክ ዓይነት) ቀምሰዋል።
በጎይታ እና በሚኒካኖቭ መካከል የሚደረገው ውይይት ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X