በአርሜኒያ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
16:13 25.06.2025 (የተሻሻለ: 16:34 25.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአርሜኒያ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
የአርመኒያ ፓሊስ ከሊቀ ጳጳስ ባግራት ጋልስትያን በተጨማሪ ሰባት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል። ከነዚህም መካከል፦
🟠 የካራባክ የፓርላማ አባል ዳዊት ጋልስቲያን፣
🟠 ጡረታኛው ኮሎኔል ሚግራን ማከሱድያን፣
🟠 የአርሜኒያ አብዮታዊ ፌዴሬሽን የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አካል አባል ኢጎር ሳርግስያን፣
🟠 ነጋዴው ቲግራን ጋልስቲያን እና
🟠 የካራባክ ጦርነት ጀግና አራ ሮስቶምያን አባትና አክቲቪስት ይገኙበታል።
የአርሜኒያ ብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት የካራባክ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ አሾት ዳንዬልያን መኖሪያ ቤት እንደፈተሸም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X