ብሪክስ መካከለኛው ምሥራቅ ከጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች የጸዳ ቀጣና እንዲሆን ጥሪ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሪክስ መካከለኛው ምሥራቅ ከጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች የጸዳ ቀጣና እንዲሆን ጥሪ አቀረበ
ብሪክስ መካከለኛው ምሥራቅ ከጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች የጸዳ ቀጣና እንዲሆን ጥሪ አቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.06.2025
ሰብስክራይብ

ብሪክስ መካከለኛው ምሥራቅ ከጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች የጸዳ ቀጣና እንዲሆን ጥሪ አቀረበ

"ብሪክስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ በተካተቱት መርሆች መሠረት በቀጣናው ዘላቂ መረጋጋትን ለማምጣት፣ ዓለም አቀፍ ሰላምንና ደኅንነትን ለማጠናከር እንዲሁም ዲፕሎማሲና ሰላማዊ ውይይትን ለማጎልበት ቁርጠኛ ነው” ሲል የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው የጋራ መግለጫ ገልጿል።

የብሪክስ ሀገራት እስራኤል ከሰኔ 6 ጀምሮ በኢራን ላይ ያደረሰችው ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን የሚጥስ መሆኑን ዳግም ተናግረዋል።

የብሪክስ ሀገራት ውጥረቶች እንዲረግቡና ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኙ በማሳሳብ፤ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግን መሠረት በማድረግ ሲቪሎችን፣ ሲቪል መሠረተ ልማቶችንና ሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ሰዎችንና አካባቢን ከጉዳት ለመጠበቅ የኒውክሌር ደህንነት ሁልጊዜም መረጋገጥ አለበት፡፡ በዚህ ረገድ ክልላዊ ችግሮችን ለመፍታት ያለሙ ዲፕሎማሲያዊ ተነሳሽነቶችን እንደግፋለን” ሲል የጋራ መግለጫቸው አመልክቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0