በመጪው አሥር ዓመት ከ93 ሚሊየን በላይ ዜጎች የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበመጪው አሥር ዓመት ከ93 ሚሊየን በላይ ዜጎች የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ
በመጪው አሥር ዓመት ከ93 ሚሊየን በላይ ዜጎች የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.06.2025
ሰብስክራይብ

በመጪው አሥር ዓመት ከ93 ሚሊየን በላይ ዜጎች የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብሔራዊ የንጹህ ማብሰያ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱን የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሱልጣን ዋሊ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ10 በመቶ አይበልጥም። ይህም 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ማገዶ፣ ኩበትና ከሰልን በመጠቀም የእለት ምግቡን ያዘጋጃል ማለት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ ሲሆን 36 ሚሊየን ስቶቭ እንደሚሰራጭና የካርበን ልቀት እንደሚቀንስ ተመላክቷል።

ፍኖተ ካርታው በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎትና በማከፋፈል ዘርፎች ለ335 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል መባሉን የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0