"ለአፍሪካ ግብርና ልውጥ ህያዋን መልስ አይሆኑም" ሲሉ የግብርና ተመራማሪው አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ለአፍሪካ ግብርና ልውጥ ህያዋን መልስ አይሆኑም" ሲሉ የግብርና ተመራማሪው አስታወቁ
ለአፍሪካ ግብርና ልውጥ ህያዋን መልስ አይሆኑም ሲሉ የግብርና ተመራማሪው አስታወቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.06.2025
ሰብስክራይብ

"ለአፍሪካ ግብርና ልውጥ ህያዋን መልስ አይሆኑም" ሲሉ የግብርና ተመራማሪው አስታወቁ

ዶ/ር ፀደቀ አባተ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ የልውጥ ህያውን (GMO) የአፍሪካን ሀገር በቀል እውቀት እና ተፈጥሮ አደጋ ውስጥ ይከተዋል ሲሉ ጉዳዩ በጥንቃቄ መታየት እንዳለበት አሳስበዋል።

"አፍሪካ ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑ የሚታረሱ የሰብል ዝርያዎች እንዳሉ እናውቃለን፤ ግን እኛ አፍሪካውያን ለምርምርና ልማት በቂ ትኩረት አልሰጠንም ... አካሄዳችን መለወጥ አለበት ካልሆነ የራሱ አደጋ አለው" ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም የልውጥ ህያዋንን ምርቶች በስፋት ወደ አፍሪካ ግብርና ለማስገባት በፖሊሲ አውጪዎች እና በመንግሥት ላይ የሚደረገው ጫና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

"አህጉሪቷ የራሷን የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ግዜ የልማት አጀንዳዎች ማዘጋጀት አለባት፡፡ ነገሮች አሁን ባሉበት አካሄድ መቀጠል የለባቸውም" ሲሉ አፍሪካዊ የሆኑ መፍትሄዎች እንዲበረታቱ ጥሪ አቀርበዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0